ሙያ v1.0.0 ከመሰረታዊ ኮምፒውተር ጀምሮ እስከ አድቫንስድ ሃርድዌር ሶፍትዌር ጥገና ዌብሳይት ዲዛይን ከ ዌብ ሆስት እንዲሁም አንድ ሶኬት ወይም ማከፋፈያ ከመስራት ትልልቅ ኤሌክትሪክ ስራዋችን የሚሰሩበትን እውቀት በ አንድ ቦታ
ተግባር ተኮር አስተምሮ ለስራ ብቁ ማድረግ እና በጋራ መስራት ከሚለው አላማችን ጋር አፕሊኬሽኑ ብዙ ጥቅሞች አሉት.
ይህ አፕሊኬሽን ለ ጊዜው በ አማርኛና በእንግሊሽ የሚሰራ ሲሆን በቀጣይ ሌሎች የሀገር ውስጥ ቋንቋዎችን እንዲያካትት ይደረጋል
ረጅም ጊዜና ልምድ የሚፈልገውን እና መከራ የሚመክረውን የ ቴክኒክ ስራ ጥንቃቄዋችን ልምምዶችን ዘዴዎችን የሚያጋጥሙ ችግሮችን ከነመፍትሄው አሳይተን በትምህርቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እናደርጋለን
ምን ልግዛ ? የት ነው ሚሸጠው ? ምን አይነት ነው ? ማለት ቀረ ትምህርቱ ላይ ሁሉም አለ በተጨማሪም በደንበኛ አገልግሎት መስመር ላይ ቀጥታ ያገኙናል
ቴክኒካል ስራ ያለኮምፒውተር ይበራል ግን አያደምቅም እንደማለት ነው ዲዛይን ሂሳብ ስራ ፕሮፖዛል ዝግጅት እና ሌሎችንም ያገኛሉ
እውነት ነው ካልሰሩበትና ካልተለማመዱት ሁሉም ነገር ይረሳል በድጋሚ ወጪ ከማውጣት ግን መፍትሄው ይህን አፕሊኬሽን መጠቀም ነው
ስራ ጠፍቷል ወይም ይጠፋል ብለን አናምንም የጠፋው አለመተዋወቅ አለመተማመን ነው የኮምፒውተር ስራ የ ዌብሳይት ስራ የ ኤሌክትሪክ ስራ የ ካሜራ ስራ ሲኖር ያናግሩን በጋራ እንሰራለን
የሚፈልጉትን ትምህርት ይምረጡ
ስም ስልክና የሚስጥር ቁጥር በማስገባት ይመዝገቡ
ክፍያውን ፈፅመው ደረሰኝ ይላኩልን ወዲያውኑ ትምህርቱን ይጀምራሉ
ተግባራዊ እና ስራ ምናገኝባቸውን ሙያዎች በመፅሃፍ እና ሰርቶ በሚያሳይ ቪዲዮ የታገዙ ትምህርቶችን ማስተማር እንዲሁም ድጋፍ እና ክትትል በማቅረብ ሁሉም ባለበት ትምህርቶቹን እንዲከታተል ማድረግ በተጨማሪም በ እያንዳንዱ በሚሰጡ ሙያ ትምህርቶች ላይ ጠንካራ ተሳትፎ እንዲፈጠር በማስቻል በስራና በሌሎች ጉዳዮች ላይ የጋራ ተጠቃሚ የምንሆንበትን መነገድ መፍጠር .
በትክክል ብቁ ያደርጋል የማንሰራበትን እና ተጠቃሚ ያልሆንበትን ሙያ አናስተምርም ሁሉም ትምህርቶች ላይ አንድም የተደበቀ ወይም የሚቀር አይኖርም ከ ጀማሪ እስከ ብቁ ባለሙያ ድረስ ስራ ላይ ያሉትን አንድ በአንድ ለማወቅ ያስችለናል.
በትክክል ተግባራዊ ነው እያንዳነዱ ርዕስ ትምህርቱን ለመጨረስ ሳይሆን የተዘጋጀው ሁሉም ምዕራፍ ተግባራዊ ትምህርት መስጠት ብቻ ሳይሆን ስራ ላይ በምንገባበት ወቅት እቃ ተበላሽቶብን ኪሳራ ውስጥ እንዳንገባ ወይም ቴክኒኮችን ባለማወቅ ጊዜ እንዳናባከን ጠቃሚ ምክሮችን የያዘ ነው በተጨማሪ ሙያ ከላይ ከላይ ብቻ ሳይሆን አስፈላጊ እቃ ለደንበኛ በሚገባ መልኩ ከማቅረብ እስከ ስራውን በጥንቃቄ እና በጥራት እስከ መስራት ይደርሳል ሁሉም ትምህርቶች ይሄንን ታሳቢ ያደረጉ ናቸው.
በ pdf አንሰጥም አላማችን ትምህርቶቹን በ ፅሁፍ በምስል እና በ ቪዲዮ የታገዘ ትምህርት ከማቅረብ ባለፈ በቂ ክትከትል እና ድጋፍ ለመስጠት አመቺ ሆኖ ያገኘነው አፕሊኬሽን ነው.
በትክክል ስራ ፈለግ ፈለግ ማድረግ ይፈልጋል ይሄን ለማድረግ ግን በራስ መተማመን ይጠይቃል በራስ መተማመን ደሞ አስተማማኝ እውቀት እና ድጋፍ ይፈለጋል በዚህ አፕሊኬሽን እውቀትም ድጋፍም አለ
ከ telegram ቻናል ሁሉም አስፈላጊ ሶፍትዌሮች እንዴት እንደምንጭን ከሚያሳይ መመሪያ ጋር በ እናቀርባለን ለምሳሌ ሶፍትዌር ጥገና በ አፕ ትምህርቱን ስትጀምሩ ወደዚህ ቻናል እንድትገቡ እናደርጋለን
በትክል ይሰራል ኢንተርኔት በ አንዳነድ ቦታዎች ላይሰራ ወይም ኔትዎርክ እንደሚያስቸግር ታሳቢ በማድረግ አንድ ጊዜ በ ኢንተርኔት ከከፈትነው በዋላ በቀጣይ መፅሃፍቶች ያለ ኢንተርኔት መከታተል ያስችለናል ቪዲዮ እና ምስል ኢንተርኔት ይፈልጋል
በጣም ጥሩ በዚህ አፕሊኬሽን በተለይ ሃርድዌር ላይ ያሉት ትምህርቶች ኮምፒውተር ጥገና ላይ ብቻ ሳይሆን ጠቅላላ ኤሌክትሪካል እና ኤሌክትሮኒክስ ላይ በቂ አውቀት እንዲኖረን ያስችላል በተጨማሪም በዚህ አፕ በፈለግነው ሰአት ትምህርቶቹን መከለስ እና ማስታወስ የምንችልበት ነው ትምህርቱን ረስተን እንደገና ለትምህርት ወጪ አናወጣም
ለሶፍትዌር ትምህርቶች አዎ በዚህ አፕ በመማር እና በኮምፒውተራችን በመለማመድ እንዲሁም ግልፅ ያልሆኑትን እርዳታ ላይ በመጠየቅ ባለሙያ መሆን ይቻላል ለ ሃርድዌር ትምህርቶች በተለይ ጀማሪ ከሆንን በ አካል ተገኝቶ መማርን አይተካም አዲስ ስንሆን በእጃችን እየነካካን መለማመድ ስላለብን በተጨማሪ ጥንቃቄ ለሚፈልግጉት ኤሌክትሪካል እና ኤሌክትሮኒክስ ሙያዎች የቅርብ ክትትል ይፈልጋሉ ከዚህ ካለፈ ማለትም እጃጅንን ካፍታታን እና ጥንቃቄዎቹን በሚገባ ከተረዳን ባለንበት ቦታ ትምህርቱን መከታተል እንችላለን
ከ ሃርድዌ ይልቅ ሶፍተዌር ተደጋጋሚ ለውጦች ይኖሩታል ይሄን ታሳቢ ሰላደረግን የሚኖሩ ለውጦችን ተከታትለን ሰለምናቀርብ ከ አፑ ትምህርት ላይ መመለከት ይቻላል
አሁን ላይ ስራ ልምምድ የምንሰጠው ለ ኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ሰልጣኞች ሲሆን በቀጣይ ሁሉም ለማዳረስ እንሰራለን
አሁን ባለበት ደረጃ ትምህርቱ በአማርኛ የቀረበ ሲሆን ቀጥሎ በሚመጣው ማሻሻያ ላይ በ እንግሊዝኛ ምርጫ ይኖረዋል እንዲሁም በሌሎች የሃገራች ቋንቋዎች ተተርጉሞ ይቀርባል
ለሚነሱ ማናቸውም ጥያቄዎች አፕሊኬሽኑ ላይ እርዳታ በሚለው ስር telegram,Whatsapp,email በስልክ መጠየቅ ይቻላል አፋጣኝ መልስ እንሰጣለን
አዎ ይቻላል
ለ ሃርድዌር ትምህርቶች የሚሆን የልምምድ እና የተግባር ፈተና ቦታ ይኖራል ራሳችንን የምንፈትንበት ጥያቄዎችን በ አፑ ላይ ይኖራሉ ሰርተፊኬት ይኖራል የሶፍትዌር ትምህርቶች በብዛት ይኖራሉ እርዳታና ድጋፍ አሰጣጥ በበለጠ ይሻሻላል የስራ እድል እና ስራ ላይ ልምምድ በሰፊው ይመቻቻል የጋራ ውይይት እነዲሁም የልምድ ልውውጥ የሚኖርበት መድረክ ይመቻቻል ስራዎችን በጋራ የምንሰራበትን መንገድ አጠናክርን እንቀጥላለን
1.በቪዲዮ የታገዘ ተግባራዊ ትህርቶች 2. በማንኛውም ሰአት ተመልሰን የምናገኘው መፅሃፍ 3.ባለንበት ቦታ ትምህርቶችን የምንከታተልበት 4. በትምህርቶቹ ላይ እና ስራ ላይ ሙያዊ ድጋፍ የምናገኝበት 5. አነስተኛ ክፍያ
አዎ አፕሊኮሽኑ የሚሰራው መጀመሪያ በተመዘገብንበት ቀፎ ነው ግን ቀፎ ከቀየርን የሚስጥር ቃል በመቀር ከበፊቱ ቀፎ አንስቶ ከአዲሱ ጋር ማስተሳሰር ይቻላል
አሁን ላይ አፑ ለ አንድሮይድ ነው የሚሰራው በቀጣይ በሚመጡት ማሻዎች አይፎን ላይ እንዲሰራ ይደረጋል
Peachtree Accounting, Mobile App Development ,ሞባይል ጥገና ቲቪ ጥገና
በትክክል አላማውም እሱ ነው አፑን ካወረዳችሁ በኋላ ከ ክፍያ በፊት የትምህርቱን ይዘት መኒገባ ማየት ይቻላል